Uncategorized

በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ማማ ወረዳ ዘካሪ፣መከሪ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ለዘላቂ ሰላም በሚል መሪ ቃል ከሃይማኖት አባቶችና ከሃገር ሽማግሌዎች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ ።

በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ማማ ወረዳ ዘካሪ፣መከሪ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ለዘላቂ ሰላም በሚል መሪ ቃል ከሃይማኖት አባቶችና ከሃገር ሽማግሌዎች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ ።

ሞላሌ ህዳር 13/2018ዓ.ም ( መ/ማ/መኮጉ ፅ/ቤት) በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ማማ ወረዳ ዘካሪ፣መካሪ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ለዛላቂ ሰላም በሚል መሪ ቃል ከሃይማኖት አባቶችና ከሃገር ሽማግሌዎች ጋር የውይይት መረክ ተካሂዷል ።

የወረዳው አስተዳደር ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ አረጋኸኝ በቃኸኝ፣ የትምህርት ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ጥበቡ ታደሰ፣የግብርና ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ማንደፍሮ አየናቸው በወረዳችን የተጀመሩ ልማቶች እድንጨርስ ፣ያለውን አንጻራዊ ሰላም እንዲቀጥል አባቶች ልትመክሩንና ልታስተምሩን ይገባል ሲሉ የመወያያ ሃሳብ አቅርበዋል ።

ከቀረበው ሃሳብ በመነሳት ሃገር ሰላም እንዲሆን እንፈልጋለን ፣ ሰላም ከሌለ ሁሉም ነገር የለም ።ሰላም እዲሰፍን ልማት እንዲስፋፋ በየሃይማኖት ተቋማቶችና በየእድር ቤቶች እናስተምራለን ፣ እንመክራለን ፣ መንግስት እንደ መንግስት ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ትኩረት ሰጥቶ መፍታት አለበት ሲሉ ገልፀዋል ።

LEAVE A RESPONSE

Your email address will not be published. Required fields are marked *