ለመጪው የክረምት ወቅት በቂ ቅድመዝግጅት እየተደረገ ነው።
ሞላሌ ጥር 20/2018ዓ.ም(መማመኮጉ)በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ማማ ምድር ወረዳ በአምቦውሃ ችግኝ ጣቢያ በዘመናዊ የግብርና ልማት ስርዓት እየለማ ያለ ችግኝ ተጎብኝቷል።
በጉብኝቱ የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ተክለየስ በለጠ፣የሰሜን ሸዋ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ሀላፊ አቶ ተማለደ በላይሁን፣የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ምክትል ኃላፊ ኮማንደር እምሻው አካለ፣ የሞላሌ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ አቶአብርሃም አድምቄ፣የ104ኛ ክፍለጦር አመራር ሻለቃ ውብሸት ታመነና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት የችግኝ ጣቢያ ዝግጅት ተጎብኝቷል። በአጠቃላይ አስራ ምስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ችግኝ ለማፍላት እቅድ ተይዞ ከዚህ ውስጥ ዘጠኝ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ችግኞች የተፈጥሮ ሃብት ተፋሰሶችን በአረንጓዴ አሻራ ለመሸፈን የተዘጋጁ መዘጋጀታቸውን ከወረዳው ግብርና ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል። ከዚህ ጎን ለጎንም የአፕል ምርትን ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ እንደሆነም ተጠቁሟል።














