Uncategorized

ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ የግማሽ አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ፣ የአባላት ተሳትፎና የሃብት አሰባሰብ የኮሙዩኒኬሽን እቅድ ትውውቅ አደረገ።

ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ የግማሽ አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ፣ የአባላት ተሳትፎና የሃብት አሰባሰብ የኮሙዩኒኬሽን እቅድ ትውውቅ አደረገ።

ሞላሌ ጥር 26/2018ዓ.ም(መማመኮጉ) የመንዝ ማማ ወረዳ አልማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የግማሽ አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ፣ የአባላት ተሳትፎና የሃብት አሰባሰብ የኮሙዩኒኬሽን እቅድ ትውውቅ አድርጓል።

በእቅድ ትውውቁ የወረዳና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮችና የአልማ ኮሚቴዎች ተሳትፈዋል።

በአፈፃፀም ግምገማውና እቅድ ትውውቁ ወቅት አልማ በወረዳውና ከተማ አሰተዳደሩ ዘመናዊ ግንባታ የገነባበት አንቡላንስ ያሟላበት በየዘርፉ ገደብየለሽ ልማት ያሟላ ትልቅ የልማት አርበኛ ነው።ስለዚህ በየተቋማት ያሉ ባለሙያዎችንና ተቋማትን እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን አሟጦ አባል ማድረግ፤የራስን የመልማት ፍላጎት በራስ ማልማት መቻል አለብን ብለዋል።ሰለአልማ ብዙ ማውራት ለቀባሪው ማርዳት ነው ትናንት የተሰሩ ተግባራት ማሳያዎች ናቸው።ስለዚህ ግንባር ቀደም ሆነን መስራት አለብን። አባል መሆናችንም ህዝባዊነታችንን ማሳያ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

የአልማ ኮሚቴ በየደረጃው ያለው አመራር ለዚህ ተግባር ትኩረት ሰጥቶ መስራቱ እናመሰግናለን።ሃምሳ ሎሚ ለአንድስው ሸክም ለሃምሳ ሰው ጌጡ ነው እንደሚባለው ሁሉንም አካል አባል ማድረግ ልማትን ማፋጠን ተገቢ ነው።መንግስት የያዘውን የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን የመጨረስ እቅድም ከግብ ለማድረስ አልማን መደገፍ ግድ ነው ያው ኮሚቴው በየደረጃው ግንዛቤ ማስጨበጥ የቀጣይ አቅጣጫ እያስቀመጡ መሄድ ያስፈልጋል ሲሉ አሳስበዋል።

በመጨረሻም የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ መርሻ ሀይሉ፣የሞላሌ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ አብርሃም አድምቄና የአልማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ወንድምአገኝ ይርጋ በሰጡት ማጠቃለያ ተግባሩን አስተባብሮና ትኩረት ሰጥቶ መምራት ፍትሀዊ በሆነ መዋጮ ፍትሀዊ ልማትን ተደራሽ ማድረግ ተገቢ መሆኑን አስረድተዋል።አባል ያልሆኑትን አባል ማድረግ በየቀበሌው ያልተመለሱ ካርኔዎችን የማስመለስ ስራ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ የቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠው አጀንዳው ተጠቃሏል።

LEAVE A RESPONSE

Your email address will not be published. Required fields are marked *