ሞላሌ: ጥር 11/2018 ዓ.ም (መማመኮ) የሞላሌ ከተማ አሰተዳደር ሰላምና ደህንነት ፅህፈት ቤት የከተራና የጥምቀት በዓል በሰላም መከበራቸውን አስታወቀ።
የፅህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ እንግዳሰው ታለጌታ በሞላሌ ከተማና አካባቢው ትናንት ታቦታቱ ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው ወደ ጥምቀተ ባሕር ወርደዋል።
በዛሬው እለትም ታቦታት ከጥምቀተ ባሕር ወደ ማዳሪያቸው ተመልሰዋል።በዓሉ ስኬታማ እንዲኾን በቅንጅት መሠራቱን ተናግረዋል።
ሀላፊው አያይዘውም በዓሉ ስኬታማ እንዲኾን የፀጥታ አካላት፣ አመራሮች፣የሃይማኖት አባቶች፣ ወጣቶች እና ህዝበ ምዕመኑ የተጫወቱት ሚና ትልቅ መኾኑንም አስረድተዋል። ለእነዚህ አካላትም ትልቅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።













