ግምቱ ከ2ሚሊዮን 500ሺህ ብር በላይ የሆነ የህክምና መሳሪያ እና የቢሮ ዕቃ ድጋፍ ተደረገ።
ሞላሌ ህዳር 12/2018ዓ.ም(መማመኮጉ) ግምቱ ከ2ሚሊዬን 500ሺህ ብር በላይ የሆነ የህክምና መሳሪያ እና የቢሮ ዕቃ ድጋፍ መደረጉን የመንዝ ማማ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት አስታወቀ።
የፅ/ቤቱ ሀላፊ አቶ ተክለአብ አስበ እንደገለፁት ድጋፉን ያደረገው የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ሲሆን ለሸሾ አጠቃላይ ጤና ኬላ ፍሪጅ፣ዘመናዊ የህክምና አልጋዎች፣የህክምና ማጣሪያዎች፣ዘመናዊ ደሊቨሪ ኮች እና የፅዳት እቃዎች ናቸው ብለዋል። ድጋፉ አጠቃላይ 2ሚሊዬን 500ሺህ144 ብር ነው ሲሉ ገልፀዋል።
ሀላፊው አክለውም ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው ድጋፉ በጤናው ዘርፍ አጠቃላይ ጥራቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።












