ከጣርማ በር መለያ ሰፌድ ሜዳ ሞላሌ ወገሬ ሊሰራ የተጀመረዉ የአስፋልት መንገድ ባለመሰራቱ ለከፍተኛ እንግልትና ወጪ ዳርጎናል ሲሉ የሞላሌ ከተማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ቅሬታቸዉን አሰሙ፡፡ አመራሮች በበኩላቸዉ በመሪነት ሚናቸዉ ላይ ጫና ማሳደሩን ተናግረዋል፡፡
ከጣርማ በር መለያ ሰፌድ ሜዳ ሞላሌ ወገሬ ሊሰራ የተጀመረዉ የአስፋልት መንገድ ባለመሰራቱ ለከፍተኛ እንግልትና ወጪ ዳርጎናል ሲሉ የሞላሌ ከተማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ቅሬታቸዉን አሰሙ፡፡ አመራሮች በበኩላቸዉ በመሪነት ሚናቸዉ ላይ ጫና ማሳደሩን ተናግረዋል፡፡
ሞላሌ ህዳር 2/2018ዓ.ም (መማመኮጉ)ከጣርማ በር መለያ ሰፌድ ሜዳ ሞላሌ ወገሬ ሊሰራ የተጀመረዉ የአስፋልት መንገድ ባለመሰራቱ ለከፍተኛ እንግልትና ወጪ ዳርጎታል ሲሉ የሞላሌ ከተማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ቅሬታቸዉን አሰሙ፡፡ አመራሮች በበኩላቸዉ በመሪነት ሚናቸዉ ላይ ጫና ማሳደሩን ተናግረዋል፡፡
የሞላሌ ከተማ ነዋሪና የአሽከርካሪ ባለንብረት የሆኑት አቶ ደምሴ ሸዋፈራ መንገዱ በየቦታው በመቆፋፈሩ ሁለት ሰዓት የሚወስደው ጉዞ ወደስምንት ሰዓት እንዲራዘም አድርጎታል። የተሽከርካሪ እቃ እየተሰበረ ተጨማሪ የመኪና ወጪ እያወጣን ነዉ ።በጊዜዉ የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ መንግስት ችግራችንን ሊፈታልን መስሎን ነበር ነገር ግን የባሰ መከራ ዉስጥ ነዉ የከተተን ፣በዚህ ምክንያት ብዙ ጊዜ አቤቱታ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድረስ ዉክልና ይዘን ሄደን ጠይቀናል። ነገር ግን የተሰጠን ምላሽ አጥጋቢ እይደለም ።ወይ በፊት እንደነበረው ተመልሶ ይስተካከልልን።በዚህ ምክንያት አካባቢያችንን ጥለን ለመሄድ እየተገደድን ነዉ ሰሚ አካል ካለ ምላሽ ቢሰጠን ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
ሌላኛዉ የከተማ ነዋሪና በንድግ ስራ የሚተዳደሩት አቶ ዘነበ ተክለሀይማኖት በበኩላቸዉ በንግድ ስራቸዉ ላይ ጫና እንዳሳደረባቸዉ ተናግረዋል፡፡ የማስጨኛ ዋጋ ስለሚጨምር ህብረተሰቡ በኑሮ ዉድነት እንዲጋለጥ አድርጎታል። መንግስት በሌላዉ አካባቢ እንደሚሰራዉ ሁሉ ለምን የመንዝን ህዝብ ችግር አይፈታልንም ሲሉ አሳስበዋል፡፡
የመንግስት ሰራተኛ የሆኑት አቶ ዘነበ ጠለምህረት በመንገዱ መጓተት ምክነያት መንግስት ሰራተኛዉ ለከፍተኛ ኑሮ ዉድነት ተጋልጧል። በአሰበዉ ጊዜና ሰዓት ወጥቶ መግባት አልቻለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የወረዳዉ የመንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሽመልስ ፅጌ በመንገዱ አለመመቸት ምክንያት ትርፍና ታሪፍን ማስከበር አልተቻለም።ለመስራት ውል የያዘው ኮንስትራክሽን በየቦታው እየቆራረጠ በማበላሸቱ መንገዶችን ለመጠገን ማሽን ማስገባት አልተቻለም። መንግስት አፋጠኝ ምላሽ ሊሰጠን ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
የወረዳዉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ ቀፀላ ከበደ በበኩላቸዉ ህዝቡ በየጊዜዉ ጥያቄዉን ያነሳል ።ምላሽ መስጠት አልቻልንም፡፡ ችግሩን እስከ ም/ል ጠቅላይ ምኒስትሩ አድርሰንዋል። ግን ምንም የተሰጠን ምላሽ የለም በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬት አሳድሮብናል ብለዋል፡፡
የሞላሌ ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ አብርሀም አድምቄ መንገዱን በ36 ወራት አጠናቀዉ ሊያስረክቡ ነበር የመሰረት ድንጋይ የተጣለዉ ነገር ግን ከተጀመረ ሰባት ዓመታትን አስቆጥሯል። ነባሩን መንገድ በማፍረሳቸዉ በዚያ መስመር ለመጓዝ ችግር ፈጥሯል። በንግድ ስራ ላይ መስተጓጎልን በመፍጠሩ የኑሮ ዉድነቱ ጣራ እንዲነካ አስችሎታል ብለዋል፡፡ከንቲባዉ ህዝቡ በለዉጡ ያገኘዉን የልማት ፍንጭ በለዉጡ መንግስት ተጠናቆ ማየት ይፈልጋል፡፡ በዚህ የተነሳ እንደመሪም ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጫና አሳድሯል፡፡ጥያቄዉን ለበላይ መንግስት ያሳወቅን ቢሆንም አሁንም ለመስራት ዝግጅት እንደሌለ የተገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ። መሪዎች እንደ መሪ የህዝቡን ጥያቄ መመለስ ካልቻልን ለመምራት እየተቸገርን ነው።በየደረጃው ያለው መንግስት ይህን የህዝብ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጠን ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
የመንዝ ማማ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መርሻ ሀይሉ በበኩላቸዉ መንገዱ 118 ኪ.ሜትር ርዝመት ያለዉ ሲሆን 60 በመቶ ያክሉ የሚያልፈዉ በወረዳዉ ላይ ነዉ ።ከዚህ ጋር ተያይዞ ለ219 አርሶ አደሮች በጊዜዉ በነበረዉ ገበያ ተሰልቶ 233ሚሊዬን 500ሺህ ብር ካሳ ክፍያ እንዲሰጣቸዉ ተወስኖ ነበር፡፡ ከፍያዉ አስካሁን ሳይሰጣቸዉ መንገዱም በአግባቡ ሳይሰራ በየቦታዉ ተቆፍሮ ከአገልግሎት ውጭ ሆኗል። አርሶ አደሮቹም የካሳ ክፍያዉ አሁን ባለው የገበያ ዋጋ ይተመንልኝ እያሉ በየቀኑ ቅሬታ ያቀርባሉ ምላሽ መስጠት አልቻልንም ብለዋል፡፡ በየጊዜዉ ይሰራል ተብሎ የገባዉ ሬንጅ እየቀለጠ በአካባቢዉ ያለዉን ውሃ እየበከለ ለሌላ ተጨማሪ ቀውስ እየተዳረግን ነዉ እንደመሪም መውጫ መግቢያ ያሳጣን ችግር ነው የበላይ አካል አስቸኳይ መፍትሄ ለሰጠን ይገባል ሲሉ ጥያቄያቸውን በምሬት አንስተዋል፡፡
ተቋማችን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን በጊዜው የመሰረት ድንጋይ ሲጣል ቦታው ላይ ተገኝቶ ነበር።የነበረውን የመንዝን ህዝብ ከልብ የመነጨ ደስታ እንግዳ ተቀባይነት በወቅቱ የመሰረት ድንጋይ ለማስቀመጥ ለመጡት ለመንገድ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ አቀባበል አድርጎ አመስግኖ ሸኝቷል።አሁን ደስታው ወደ ሀዘን ተቀይሯል። ስለምን መንግስት የዚህን ምስኪን ህዝብ ችግር መፍታት ተሳነው።ጥያቄያችን ነው ????????















