የመ/ቤቱ ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ እሴቶች
ራዕይ
- ሰብአዊና ዴሞክራሴያዊ መብቶች የተረጋገጡበት፣መልካም አስተዳደር የሰፈነበት፣በሁሉም የልማት መስኮች ፈጣን እድገት የተመዘገበበት እና ድህነትን ታሪክ ያደረገ ወረዳ ተፈጥሮ ማየት፤
ተልእኮ
- የዲሞክራሲ ተቋማትና የመልካም አስተዳደር አደረጃጀትን ማጠናከር ፣የክትትል ድጋፍ ተግባራትን ማጠናከር
- ልማትን ለማፋጠን የሚወጡ ህጎችን መፈፀምና አፈፃፀማቸውን መከታተል
- ለመንግስታዊተቋማት፣ለሲቪክማህበራት፣ለዜጎች፣ለመካከለኛናዝቅተኛውአመራር ሁለንተናዊ የድጋፍ አገልግሎት መስጠት
የጽ/ቤቱ እሴቶችና የሥራ መርሆዎች
- በየደረጃው ብቃት ያለው አመራር ለመፍጠር ጠንክረን እንሰራለን፡፡
- ህዝባዊ ወገንተኝነትን በስራ እናረጋግጣለን፡፡
- የወጡና የሚወጡ ህጎች ተግባራዊ እንዲሆኑ እንሰራለን፡፡
- የህግ የበላይነትን እናከብራለን፡፡
- የባለጉዳዮችን ጥያቄ በጥሞና እናዳምጣለን፣በወቅቱ ተገቢውን ምላሽ እንሰጣለን፡፡
- በእኩልነት ላይ የተመሰረተ የስርዓተ ፆታ መርህን እንከተላለን፡፡
- የህብረተሰቡን እና የመ/ቤቱን ሰራተኞች ዴሞክራሴያዊ ተሳትፎ ያረጋገጠ አሰራር እንከተላለን፡፡
- የግለሰቦችን ጥረትና ተነሳሽነት እንዲጎለብት ጠንክረን እንሰራለን ፡፡
- ተደጋግፎ የመስራት ባህልና መተማመን በመስሪያ ቤቱ እንዲሰፍን እናደርጋለን ፡፡
- የግለሰብና የቡድን መብትን እናከብራለን፡፡
- አላስፈላጊ የሆነ ኪራይ ሰብሳቢነትን በቁርጠኝነት እንታገላለን፡፡
- ግልፀኝነትና ተጠያቂነት የስራችን መሪ ይሆናሉ፡፡
የተቋሙ ሥልጣንና ተግባር
ተቋሙ በተቋቋመበት አዋጅና ደንብ እንዲሁም ከተሰጠው ስልጣንና ተግባር አኳያ ከሚያከናውናቸው በርካታ ተግባራት ውስጥ፡-
የህዝብ ጉዳዮች ተፈጻሚነትን በመደገፍ ተቋማትንና አደረጃጀቶችን በማስተባበር በጠራ መረጃ ላይ በመመስረት የህብረተሰቡን ፍላጎት ለማሟላትና ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ በጽናት የሚሰራ ተቋም ነው፡፡ህቭጅብህግክጅ
መንግስት የሚያወጣቸውን ህጎችና መመሪያዎችን ተፈጻሚነት መከታተል ተፈጻሚ እንዲሆኑ ማድረግ
ከወረዳ እስከ ቀበሌ ድረስ የሚገኙ የመንግስት መዋቅሮችንና አስፈጻሚዎችን ድጋፍና ክትትል ማድረግ
ከወረዳ እስከ ቀበሌ ድረስ የሚዘጋጁ የኢኮኖሚ ፣የማህበራዊ ልማትና የመልካም አስተዳደር እቅዶችን ተገቢነት መደገፍና መከታተል
የተዘጋጁ እቅዶችን አፈጻጸም በመደገፍ ፣በመከታተልና በመገምገም ከፍተቶችን እየለዩ የማስተካከያ ግብረ-መልስ መስጠት
በየደረጃው የሚነሱ የመሰረተ ልማትና ተያያዥነት ያላቸውን የመ/አስተዳደር ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ እንዲያገኙ ክትትል ማድረግ
መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ እንዲሁም ባለሀብቶችን በልማት ስራ ላይ በማሳተፍ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ
በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ከፍ ከማድረግ ለህብረተሰቡ የሚጠቅም የስልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እንዲሰሩ ማድረግ
በአጠቃላይ የወሳኝ ኩነት ምዝገባዎች ውጤታማነትን ከፍ ማድረግ